ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር ከ9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራቱን አስታወቀ!! አዲስ አበባ፦ ታህሳስ 16 / 2018 ዓ.ም

ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር ከ9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራቱን አስታወቀ!!

ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር አጠቃላይ ሀብቱ ከ9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ።

ባንኩ 4ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ከበደ የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል።

ባንኩ በበጀት ዓመቱ አበረታች የፋይናንስና የሥራ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ርዕሰ መስተዳደሩ ጠቁመዋል።

የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን መድረሱን የገለፁት አቶ ጥላሁን፤ የካፒታል መጠኑ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሆኑን አመላክተዋል።

በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 213 ሚሊዮን ብር ትርፍ መገኘቱን ነው የገለፁት።

331 ሺህ 788 አዲስ ደንበኞችን በማፍራት አጠቃላይ የቁጠባ ደንበኞችን 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

ይህም የባንኩን የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ወደ 6 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል ማስቻሉን ገልፀዋል።

በግብርና፣ ንግድ እንዲሁም በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራዝ ዘርፎች ለተሰማሩ ደንበኞች ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መሰራጨቱን ርዕሰ መስተዳደሩ ጠቁመዋል።

ባንኩ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 241 በማሳደግ ተደራሽነቱን ማስፋቱን ነው የገለፁት።

በ2018 የዲጂታል ፋይናንስና የዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎትን ማስፋት፣የካፒታል መጠንና የጥሬ ገንዘብ አቅምን ይበልጥ ማጠናከር የባንኩ ተቀዳሚ ተግባራት እንደሆኑ አቶ ጥላሁን አስገንዝበዋል።

ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2035 የምስራቅ አፍሪካ ባንክ የመሆን ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል።

የሁላችንም ባንክ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *