ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግ የብድር አቅርቦትን በቀጣይ የማመቻቸቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኦሞ ባንክ አስታወቀ።

‎ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም
‎ባንኩ የ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀምን ከዲስትሪክትና ከቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ጋር በሀዋሳ ከተማ የምክክር መድረክ አካሄዷል።

‎በምክክር መድረኩ የኦሞ ባንክ ተ/ፕሬዝዳንት አቶ አለማየው ኃ/ጊዮርጊስ እንደገለፁት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉት ማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በተለይም በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ እንዲሰማሩ ቀጣይነት ያለውን የብድር አቅርቦትን በማመቻቸት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በትጋት ባንኩ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

‎ከዚህ በፊት በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የነበሩ ልምዶችን አጠናክሮ በመቀጠል ባንኩን ተወዳዳሪ ለማድረግ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው የገለፁት የባንኩ ተ/ፕሬዝዳንት የቤት ለቤት የቁጠባ ስራን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

‎በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና ስራ አጥነትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኦሞ ባንክ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

የደንበኞችን እርካታ ለማረጋገጥ በርካታ ተቋማዊ የሪፎም ስራ ሲሰራ የቆየው ባንኩ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እንዲሁም ቁጭት ጭምር ለተሻለ የለውጥ ስራ ተግቶ ለመስራት አቅጣጫ ማስቀመጡን የባንኩ ተ/ፕሬዝዳንት ገልፀዋል፡፡

በሚቀጥሉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የባንኩን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማረጋገጥና በኢንዱስትሪው ውስጥ ጠንካራና ተወዳዳሪ ለማድረግ ለደንበኞቹም ብቃትና ጥራት ያለውን የፋይናንስ አገልግሎትን ለመስጠት እንደሚያስችሉ የተጠኑት አስራ አራት ስትራቴ ጂዎች በባንኩ ኮርፖሬት ስትራቴጂና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ም/ል ፕሬዝዳንት በዶ/ር ፍሬው በቀለ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያትም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እስከ እያንዳንዱ ሠራተኛና ባለድርሻ ድረስ በማውረድ እንደሚተገበርም አስረድተዋል።

ባንኩ በሁለት ቀን የምክክር መድረክ ቆይታው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሀብትን ለማሰባሰብና የደንበኛን እርካታ ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም በአክሲዮን ሽያጭ፣ እንዲሁም ደንበኛን በማወቅ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን፣ በብድር ስርጭትና አመላለስ ላይ ትኩረት በማድረግ ማብራሪያና ውይይት አድርጓል፡፡

በመጨረሻም በተግባር አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የብር፣ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሸልሟቸዋል፡፡

ባንኩ ካሉት 241 ቅርንጫፎች መካከል ከወልቂጤ ዲስትሪክት የካምፕ ቅርንጫፍ 1ኛ፣ እሬሻ ቅርንጫፍ 2ኛ፣ እንዲሁም ከወራቤ ቅርንጫፍ 3ኛ ለወጣው ወራቤ ቅርንጫፍ ባንኮች የተለያየ የብር መጠን፣ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት አበርክቷል፡፡

ከዲትሪክቶች ወልቂጤ ዲስትሪክት 1ኛ፣ አርባምንጭ ዲስትሪክት 2ኛ፣ እና ሶዶ ዲስትሪክት 3ኛ በመውጣታቸው የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ፣ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸው የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡

‎ ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *