ለኦሞ ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች የተላለፈ የጉባኤ ጥሪ

 

ለኦሞ ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች የተላለፈ የጉባኤ ጥሪ

በኢፌዲሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ 393(2) እና 400 እንዲሁም በማህበሩ መመሥረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 16 መሠረት የኦሞ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 3ኛ አስቸኳይ እና 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ነክሴስ ሆቴል በተዘጋጀ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ ያቀርባል፡፡

  1. ማህበሩ የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
    • አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ልደታ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፤
    • የማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር MT/AA/3/0058220/2017፣
    • የባንኩ የተፈረመ ካፒታል ብር 3,210,742,000 (ሦስት ቢሊየን ሁለት መቶ አሥር ሚሊየን ሰባት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ብር)፤
    • የተከፈለ ካፒታል ብር 2,879,104፣ 790.00 (ሁለት ቢሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሚሊዮን አንድ መቶ አራት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና) ነው፡፡
  2. የ3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
    • አጀንዳ ማጽደቅ፣
    • የማህበሩን መመሥረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣
    • የስብሰባውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፡፡

 

 

  1. የ4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡
    • የጉባዔው አጀንዳ ማጽደቅ፣
    • የዳይሬክተሮች ቦርድ ጊዜያዊ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ መምረጥ፤
    • የአዳዲስ አክሲዮኖች ዝውውር ማጽደቅ፣ አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
    • የ2017 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
    • የ2017 የሒሳብ ዓመት የውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት፣ የሀብትና ዕዳ ሚዛን እንዲሁም የትርፍና ኪሣራ መግለጫ ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
    • የ2017 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ እና የ2018 ወርሃዊ አበል በሚመለከት በቀረበዉ የዉሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
    • የዓመታዊ ትርፍ ክፍፍል በተመለከተ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
    • የቦርድ አባላት ምልመላና ሹመት ሥነ ሥርዓት ሰነድ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
    • የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፤
    • የስብሰባው ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፡፡
  2. ማሳሰቢያ
    • በጉባዔዎቹ ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከስብሰባው ዕለት ከሶስት ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ናይል ኢንሹራንስ ሕንጻ 20ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የማህበሩ ጸሐፊ ቢሮ በመቅረብ ባንኩ

ለዚሁ ጉዳይ ባዘጋጀው የውክልና ቅፅ ላይ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  • ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና በጉባኤዎቹ ለመካፈል የሚያስችል ውክልና ይዛችሁ ለምትቀርቡ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፖስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
  • ምልዓተ ጉባዔዎቹ ተወያይቶ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች በጉባዔዎቹ ባልተገኙ አባላት ላይም የፀና ይሆናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

የባንኩን ድረ-ገጽ፡ https://omobanksc.com

           የፌስ ቡክ ገጽ፡ https://web.facebook.com/OMFIHQ ይጎብኙ

የኦሞ ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *