ኦሞ ባንክ አ.ማ. እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ::

ዜናአዲስ አበባ  |  ኅዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም

ኦሞ ባንክ አ.ማ. እና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ።

ዶ/ር ስምዖን ሙላት፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ፀሐፊ የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ብሩክ ዋለልኝ
ዶ/ር ስምዖን ሙላትዋና ፀሐፊ፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን አቶ ብሩክ ዋለልኝፕሬዝዳንት፣ ኦሞ ባንክ

የውይይቱ ዓላማ

የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ብሩክ ዋለልኝ ከባንኩ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽሕፈት ቤት ተገኝተዋል። በቆይታቸውም ከቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።

በጋራ ለመሥራት የተመከረባቸው ዘርፎች

ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን ሰፊ መዋቅርና አቅም በመጠቀም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ የሚከተሉት ዘርፎች ላይ በቅንጅት መሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በሰፊው መክረዋል።

የፋይናንስ ዘርፍ
የልማት ዘርፍ
የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ

የኦሞ ባንክ ቁርጠኝነት

የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ብሩክ ዋለልኝ በበኩላቸው፣ ባንኩ ከተለያዩ የልማትና የእምነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ዘመናዊና ተደራሽ የባንክ አገልግሎቶችን ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የቤተክርስቲያኗ አስተያየት

ዶ/ር ስምዖን ሙላት፦ ትብብሩ ቤተክርስቲያኗ በሀገሪቱ ዙሪያ የምታከናውናቸውን የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት፣ ይህ ትብብር ቤተክርስቲያኗ በሀገሪቱ ዙሪያ የምታከናውናቸውን የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ቀጣይ አቅጣጫ

ኦሞ ባንክ ከማኅበረሰብ አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት በማጠናከር የዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በውይይቱ ወቅት ተመላክቷል።

የኦሞ ባንክና የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን አመራሮች የውይይት ምስል

በቤተክርስቲያኗ ዋና ጽሕፈት ቤት የተካሄደው ውይይት

ኦሞ ባንክ — የሁላችንም ባንክ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *