News
ኦሞ ባንክ የተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ስኬታማ እንዲሆን የተጉ መላው ሰራተኞቹን አመሰገነ!!
ኦሞ ባንክ የተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ስኬታማ እንዲሆን የተጉ መላው ሰራተኞቹን አመሰገነ!!
ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም መልኩ ስኬታማ የሆነ ውጤት እንዲመዘገብ የተጉ የባንኩን የሥራ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞችና መላው የባንኩን ማህበረሰብ አመሰግኗል፡፡
የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ብሩክ ዋለልኝ የበጀት ዓመቱ መጠናቀቅን ተከትሎ በተዘጋጀው የምስጋና መርሐ-ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የሒሳብ መዝጊያ ተግባር በተሳካ ሁኔታና በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማጠናቀቅ መቻሉ ታላቅ ስኬት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ይህ ወሳኝ የፋይናንስ ዑደት በድል እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋጽኦ፥ በእውቀትና በላብ ለከፈላችሁት መስዋዕትነት በራሴና በባንኩ ከፍተኛ አመራር ስም ምሥጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋለ፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም በአዲሱ በጀት ዓመት የ2026/2027 ስንሸጋገር ባንካችንን በኢንዱስትሪው ውስጥ ተወዳዳሪ ሊያደርጉት የሚችሉ በርካታ ዕድሎችና ታላላቅ ስትራቴጂካዊ ግቦች ተጠቅመን በአዲስ የሥራ ምዕራፍ የደንበኞቻችንን የባንክ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፥ የዲጂታል ባንክ መሠረተ-ልማቶቻችንን ለማስፋፋትና የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ (Deposit Mobilization) አቅማችንን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል። በመጨረሻም አቶ ብሩክ ዋለልኝ ሁሉም የባንኩ ሰራተኞች በትጋትና በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ኦሞ ባንክ
የሁላችንም ባንክ!!









