አቶ ብሩክ ዋለልኝ  የኦሞ ባንክ አዲስ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ


አቶ ብሩክ ዋለልኝ  የኦሞ ባንክ አዲስ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

​የኦሞ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ  ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ካፒታል ሆቴል ባደረገው ስብሰባ፣ አቶ ብሩክ ዋለልኝን አዲሱ የባንኩ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።

በአሁኑ ወቅት ባንኩ የሚገኝበትን የዕድገት ምዕራፍና ያሉበትን ተግዳሮቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት የተመረጡት አዲሱ ፕሬዚዳንት ተቋሙን ወደ ተሻለና አስተማማኝ የዕድገት መስመር ያስገቡታል ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ26 ዓመታት በላይ እጅግ የበለፀገ የላቀ የስራ ልምድ ያላቸው፣ ከታችኛው የባንክ የስራ እርከን ተነስተው እስከ ከፍተኛ የባንክ አመራርነት (Executive Leadership) የዘለቁ ስኬታማ መሪ ናቸው፡፡
ዋና ዋና የስራ ልምዶች እና የትምህርት ዝግጅት፦
የአመራር ብቃት፡ ባለፉት ዓመታት በአቢሲኒያ ባንክ ውስጥ የዋና ስራ አስፈፃሚ (CEO) ስትራቴጂካዊ አማካሪና ረዳት (Executive Assistant to the CEO) ፣ የሰው ሀብት ልማት ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር (Executive Director, HR) ፣ እንዲሁም በተለያዩ የቅርንጫፍ ደረጃዎች (ከደረጃ 1 እስከ 4) በስራ አስኪያጅነት እና በውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ክፍል ኃላፊነት በታማኝነትና በብቃት አገልግለዋል።

የትምህርት ዝግጅት፡ በጄኔራል ማኔጅመንት የማስተርስ (MBA) ዲግሪ ፣ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም (BSc) የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በአካውንቲንግ ዲፕሎማ አላቸው፡፡ በተጨማሪም በNice ኢንሹራንስ የቦርድ አባል በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

አዲሱ ፕሬዝዳንታችን አቶ ብሩክ ዋለልኝ፣ ኦሞ ባንክ የጀመረውን ዘመናዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና ተደራሽ የባንክ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩት ይጠበቃል።
ኦሞ ባንክ
የሁላችንም ባንክ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *