News
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የመምረጫ መስፈርቶችን ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ
ቀን 22/03/2018 ዓ.ም
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የመምረጫ መስፈርቶችን ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ
ኦሞ ባንክ አ.ማ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሚያካሂደው የባለአክሲዮኖች 3ኛ አስቸኳይ እና 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 9.3 መሠረት የምርጫ መስፈርቶች ከምርጫው አንድ ወር በፊት ለባለአክሲዮኖች መገለጽ እንዳለባቸው በሚደነግገው መሠረት የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ እጩዎችን በስብሰባው እለት መጠቆምና መምረጥ እንድትችሉ ለመላው የባንካችን ባለአክሲዮኖች ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡
- ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ እና የቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
- ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያለው፣
- ከባንክ ሥራ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው መስኮች በባንኪንግ፣ በሪስክ ማናጅመንት፣ ፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በኦዲቲንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት እና በዘላቂ ኢኮኖሚ እድገት ቢያንስ በአንዱ ዘርፍ 7 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፤
- በሌላ ባንክ ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም ሠራተኛ ያልሆነ፣
- በሌሎች ከአራት በላይ በሆኑ ተቋማት ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ በመሥራት ላይ ያልሆነ
- ሀቀኛ፣ ታማኝ፣ ጠንቃቃ፣ እና መልካም ዝና ያለው እና በማጭበርበር፣ ዕምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆኑ የሒሳብ መግለጫዎች በማቅረብና በመሳሰሉት ተግባራት ተከሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣
- በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሣኔ ያልተሰጠበት እንዲሁም በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያ ያልተወሠደበት፤
- በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሒሳቡ ያልተዘጋበት፤
- ታክስ ባለመክፈል ተከሶ የጥፋተኛነት ውሳኔ ያልተሰጠበት፤
- የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም የሚመራው ወይም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የበላይ ኃላፊ የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት ወይም ያልገባበት፤
- በጠቅላላ ጉባኤ እለት በሚቋቋመው ጊዜያዊ የቦርድ ጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባል የማይሆን፤
- ሌሎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች እና በሕግ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆን ይኖርበታል፡፡
ማሳሰቢያ፡–
- በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴት ጾታም ያገልግላል፡፡
- በአጠቃለይ ከሚመረጡ የቦርድ አባላት 1/3ኛው ተጽኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በእነዚህ ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ፣ 1/3ኛው በሁሉም ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ሲሆን ቀሪ 1/3ኛው በነባር ቦርድ ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ገለልተኛ ዳይሬክተሮች (Indipendent Directors) ይሆናል፡፡
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የሚካሄደው በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው፡፡
- ቦርዱ በቂ የጾታ ስብጥር ያለው እንዲሆን ስለሚያስፈልግ ቢያንስ ሁለት ሴቶች በቦርድ አባልነት መመረጥ አለባቸው፡፡
- ቦርዱ የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ ስብጥር ያለው እንዲሆን ይፈለጋል፡፡
- ባለአክሲዮኖች ጥቆማ ሲሰጡ ስለእጩው ትምህርትና የሥራ ልምድ አጭር ማብራሪያ ለመስጠት መዘጋጀት አለባቸው፡፡
- አንድ ባለአክሲዮን ራሱን በእጩነት መጠቆም ይችላል፡፡
- መስፈርቶችን የሚያሟላ በሕግ ሰውነት የተሰጠው ተቋም/ድርጅት መመረጥ ይችላል፡፡ ነገር ግን ተቋም/ድርጅቱ ሲጠቆም ለተቋሙ/ድርጅቱ ቋሚ ወኪል ሆኖ የሚሠራ የተፈጥሮ ሰው በጥቆማው ሂደት መቅረብ አለበት፡፡
- ከማህበሩ ጸሐፊ ውጭ ያሉ እጅግ ቢበዛ ሁለት የባንኩ ሠራተኞች (ፕሬዝዳንትና ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች) ለቦርድ አባልነት ሊመረጡ ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- የባንኩን ድረ-ገጽ፡ https://omobanksc.com
የፌስ ቡክ ገጽ፡ https://web.facebook.com/OMFIHQ ይጎብኙ
የማህበሩ ፀሐፊ


