News
ኦሞ ባንክ አህጉራዊ የንግድ ትስስርን የሚያጠናክር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ
ኦሞ ባንክ የፋይናንስ አካታችነትን ለማስፋትና የኢትዮጵያ የንግድ ድርጅቶችን ከአፍሪካ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር ከአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ትሬድ ግሩፕ (AeTrade Group) ጋር ስትራቴጂያዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።
ቀን 13/2/2019 ዓ/ም
ስምምነቱ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአቅም ግንባታ፣ በፋይናንስ አቅርቦትና በዲጂታል የንግድ ትስስር ላይ የሚያተኩር ሲሆን በተለይም አዳጊ፣ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ተወዳዳሪነታቸውን እንዲያጠናክሩና የገበያ ተደራሽነታቸውን እንዲያሰፉ ያግዛል።
በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ብሩክ ዋለልኝ ትብብሩ የባንኩን ሰፊ የደንበኞች መሠረት ከቴክኖሎጂና ከአህጉራዊ የገበያ ዕድሎች ጋር በማገናኘት የፋይናንስ አካታችነትን ለማጠናከር የሚያስችል ቁልፍ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ትሬድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉዓለም ስዩም በበኩላቸው የትብብሩን ተግባራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር የጋራ የድርጊት መርሐ ግብር እንደሚዘጋጅ አስታውቀዋል።
ኦሞ ባንክ — የሁላችንም ባንክ!







