News
ኦሞ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት 2,2 ቢሊዮን ገቢ ማግኘቱን ገለጸ ባንኩ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2025/26 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባኤውን በስኬት አጠናቋል፡፡ ሐምሌ 28/2018ዓ/ም ሀዋሳ
ኦሞ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት 2,2 ቢሊዮን ገቢ ማግኘቱን ገለጸ
ባንኩ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን
የ2025/26 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባኤውን በስኬት አጠናቋል፡፡
ሐምሌ 28/2018ዓ/ም ሀዋሳ
ባንኩ በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግደርዳሪ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ይህን ተቋቁሞ በተቀማጭ ሀብት አሰባሰብ፤ አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት ፣ የተለያዩ አካላት ጋር ያለውን መልካም ግንኝነት በማጠናከር በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ አፈጻጸሞችን አስመዝግቧል፡፡
በ2018 የበጀት ዓመት 2.2 ቢሊዮን ብር ገቢ ማገኘቱን የገለፁት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ብሩክ ዋለልኝ ሲሆኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በማፋጠን 217 ቅርንጫፎችን በማዕከላዊ የመረጃ እና የባንክ ማስተሳሰሪያ ሥርዓት ማገናኘቱን አብራርተዋል ።
የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን በመዘርጋት ደንበኞች ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስችሉንም አቶ ብሩክ ገልፀዋል ።
በቀጣይም አነስተኛ እና ጥቃቅን ብድሮችን በዲጂታል መንገድ ለማሰራጨት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን አስረድተዋል ።
በበጀት ዓመቱ ከ293 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን ወደ ፋይናንስ ሥርዓቱ መቀላቀሉን ጠቁመው 96 ሺህ 160 አዳዲስ የብድር ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን አስታውቀዋል ።
ባንኩ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እንዲሁም ሴቶችን እና ወጣቶችን በፋይናንስ በመደገፍ ተቋማዊ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛልም ብለዋል።
የዲጂታል ባንኪንግ ተደራሽነትን በማስፋፋት የደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ ማሳደግ፣የሀብት ማሰባሰብ አቅምን ማጠናከር እና ጥራት ያለው የብድር አቅርቦት ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማድረስ የባንኩ የቀጣይ ትኩረቶች መሆናቸውን አስረድተዋል ።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ብሩክ ዋለልኝ ለአዲሱ በጀት ዓመት መሳካት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ በቀጣይ በጀት አመት ለታቀዱ ዕቅዶች መሳካት በጋራ ዕሴት የሁላችንም ያላሰለሰ ጥረት ወሳኝ መሆኑን አበክረው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የ2026/27 በጀት ዓመት የተሳካ የሥራ ዘመን እንዲሆን መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡
ኦሞ ባንክ
የሁላችንም ባንክ!!









