News
ኦሞ ባንክ በአለም አቀፍ የባንክ ለባንክ አገልግሎት ጋር ያለውን የግንኙነት ሥራ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸ።

ኦሞ ባንክ በአለም አቀፍ የባንክ ለባንክ አገልግሎት ጋር ያለውን የግንኙነት ሥራ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸ።
ኦሞ ባንክ ባንክ ኦፍ ቤሩት ለንደን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር በሁለትዮሽ የባንክለባንክ ሥራ ግንኙነት ዙሪያ በኦሞ ባንክ ኘሬዝዳንት ቢሮ ተወያይተዋል።
ግንቦት10/2018 ዓ/ም አዲስ አበባ
የኦሞ ባንክ ተ/ኘሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ኃ/ጊዮርጊስ በዚህ ባንክለባንክ ግንኙነት ወቅት እንደተናገሩት ባንኩን በማዘመንና ተደራሽነቱን በማስፋፋት አገልግሎቶቹ አለም አቀፍ ፋይናንስ ንግድ ሥራ ተወዳዳሪነት ደረጀ ጠብቆ እንዲሔድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል ።
የባንክ ኦፍ ቤሩት ለንደን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳፎክሊስ አርጋሮ በበኩላቸው ኦሞ ባንክ በአራቱም ክልሎች እየሰጠ ያለው ተደራሽነት መሠረት ያደረገው አገልግሎት እና በቅርቡ የተጀመረው ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን ጨምሮ ከዚህ ቀደም ኦፍ ላይን የነበሩ ቅርንጫፎችን ኦን ላይን ለማድረግ የተወሰደው ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ በዓለም አቀፍ በኩል ባለው ባንክለባንክ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነት እንዳላቸው ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለት በኦሞ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ኘሬዝዳንት ቢሮ በተደረገው የሁለቱ ባንኮች ግንኙነት መድረክ ላይ የኦሞ ባንክ ተ/ኘሬዝዳንት አለማየሁ ኃ/ጊዮርጊስ፣ ም /ኘሬዝዳንት እና የባንኪንግ ኦኘሬሽን ሀላፊ አቶ በረከት ተከተል እና የአለም አቀፍ ባንክንግ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ አዲሱ የተገኙ ሲሆን ባንክ ኦፍ ቤሩት ለንደን ባንክ በኩል ደግሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አለም አቀፍ ፋይናንስ ተቋማት ኮርፓሬት ግንኙነት ኃላፊ ተገኝተው ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
ኦሞ ባንክ
የሁላችንም ባንክ!!

