ለዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ​ ጥር 22/ 2018 (ሆሳህና)

​የሀዲያ ዞን የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ከኦሞ ባንክ ሆሳዕና ዲስትሪክት የብድር አስመላሽ ግብረ-ኃይል ጋር የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ የሁለቱ ተቋማት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በተለይም በብድር አመላለስ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
​የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሳይ ተስፋዬ በመድረኩ እንደገለጹት፤ አሰራር ለማቀላጠፍና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ አሻራ ለማሳረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

​የኦሞ ባንክ የፋይናንስና ትሬዠሪ መምርያ ሀላፊ አቶ ግርማ ደጉ እንደገለጸት ብድር ማስመለስና አጠቃላይ ተቋማዊ ትስስርን ለማጠናከር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ሀላፊው አክለውም በግማሽ ዓመቱ ባንካችን በሆሳዕና ዲስትሪክት ለሥራ ዕድል ፈጠራ እስካሁን ከ550 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱን ገልጸዋል።

በዘንድሮው ግማሽ ዓመት ብቻ ለ506 ወጣቶች 19.2 ሚሊዮን ብር ብድር መሰጠቱን አብራርተዋል።

​በመድረኩ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተመስገን ኃይሌ ብድር በማስመለስና ተቋማዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

​የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ የቀረቡትን ነጥቦች በባለቤትነት በመያዝ በቀጣይ በዘርፉ ለውጥ ለማምጣትና የብድር አመላለስ ችግርን ለመፍታት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የሁላችንም ባንክ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *